የሴኔት አባላቱ በዋናነት የ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን አካዳሚክ ካሌንደር ላይ የተወያዩ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢብራሂም ጀማል የተዘጋጀውን ካሌንደር አቅርበዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ አመታዊ የትምህርት ካሌንደሩ የተዘጋጀው በትምህርት ሚኒስቴር ደረጃ የተወሰነውን የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በማድረግ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ሰፊ የውይይት ሀሳቦች ከተነሱ በኋላ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
➩የተማሪዎች ጥሪ ነገ ነሀሴ 30/2017 ላይ የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ማስታወቂያ የምንለቅላችሁ ይሆናል።





