jinka university የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የ2017ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ገምግሟል። – jinka university

Jinka University

Knowledge for Change.

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የ2017ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ገምግሟል።

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የ2017ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ገምግሟል።

Posted By on 10/29/25 in News

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የ2017ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ገምግሟል።

“የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮ ለማስፈፀም በ2017ዓ.ም በጀት አመት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ደግሞ በማሻሻል በ2018 በጀት አመት ለውጥ ማምጣት ይገባል” የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር

ነሃሴ 9/2017ዓ.ም

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የ2017ዓ.ም የዩኒቨርሲቲውን የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ገምግሟል።

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባላት መደበኛ ስብሰባቸውን ያካሄዱ ሲሆን የዩኒቨርሲቲውን የ2017ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ግምገማ አካሂደዋል።

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክርቤት ዋና አፈጉባኤና የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2017ዓ.ም ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት ቀርበው ውይይት በማድረግ በበጀት አመቱ በጠንካራ አፈፃፀምነት የታዩትን በማስቀጠል እንዲሁም መሻሻል የሚገባቸው ተግባራትን ደግሞ ትኩረት ሰጥቶ በማስተካከል መስራት እንደሚገባ ሰብሳቢው ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር አሳስበዋል።

በውይይቱ የ2017 የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከተገመገመ በኋላ የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ ለቦርድ አባላቱ የቀረበ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በተለይም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተግባራዊ ለማድረግ ፈርሞ የተቀበላቸውን ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች (KPIs) ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዩኒቨርሲቲውን ወደፊት በማሻገር እንዲሁም የመልካም አስተዳደርን በማስፈን ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።