Back to Home
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ በቻይና ሀገር ውሃን ከተማ (Wuhan City) ሁቤይ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (Hubei University of Technology) እየተካሄደ ባለው የቻይና – አፍሪካ የፈጠራ እና የልማት ትብብር ፎረም ላይ ጂንካ ዩኒቨርሲቲን በመወከል እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ በቻይና ሀገር ውሃን ከተማ (Wuhan City) ሁቤይ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (Hubei University of Technology) እየተካሄደ ባለው የቻይና – አፍሪካ የፈጠራ እና የልማት ትብብር ፎረም ላይ ጂንካ ዩኒቨርሲቲን በመወከል እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ፕሬዚደንቱ በቻይና ሀገር ውሃን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የቻይና – አፍሪካ የፈጠራ እና የልማት ትብብር ፎረም ከተሳትፎ ባሻገር የተለያዩ የትብብር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

የፎረሙ ዋና አላማ በቴክኖሎጂ እና በኢንዱስትሪ ሽርክና፣ በዘመናዊ ግብርና፣ በሕዝብ ጤና፣ በዘላቂ ልማት እና በወጣቶች ሥራ ፈጠራ ላይ በቻይና እና በአፍሪካ የምርምር ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ድርጅቶች መካከል ትስስር ለመፍጠር ያለመ ነው።

ከፎረሙ ጎን ለጎን ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ በ 3ኛው የቻይና አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንቶች ፎረም በመሳተፍ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና የሁባይ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (Hubei University of Technology) መካከል የጋራ መግባቢያ ሰነድ ከሁባይ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ከሆኑት ፕሮፌሰር Song Xiaochun ጋር ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን በዋናነትም በጋራ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞችን መክፈት (Opening joint educational programs – MA/MSC/PhDs)፣ የሁለቱ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ልውውጥ (Academic Staff exchange) ማካሄድ፣ በጋራ ኮንፈረንስ እና ወርክሾፖችን ማዘጋጀት፣ የምርምር እና የሳይንስ ላብራቶሪዎችን መመስረት፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ልውውጥ ትብብር፣ የስራ ፈጠራ እድል ትብብርን ማስፋት እና በቻይና – አፍሪካ የ ሮድ እና ቤልት የጋራ ፕሮጀክት ማዕቀፍ አብሮ መስራትን እንደሚያካትት ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።

ከእነዚህ ትብብሮች ባሻገር ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከሁባይ የቴክኖሎጅ ዮኒቨርስቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ጅማ ዩኒቨርስቲ ጋር በቻይና – አፍሪካ የሮድ እና ቤልት የጋራ ፕሮጀክት ማዕቀፍ አብሮ ለመስራት ተጨማሪ ስምምነት ተፈራርመዋል።

Dr. Yohannes Yitbarek, President of Jinka University, represented the university at the China-Africa Forum on Innovation and Development Cooperation, currently taking place at Hubei University of Technology in Wuhan, China. During the event, he signed several cooperation agreements.

The forum aims to build partnerships among research institutions, universities, and technology companies in China and Africa. Its focus areas include technology and industrial cooperation, modern agriculture, public health, sustainable development, and youth entrepreneurship.

Alongside the main event, Dr. Yohannes participated in the 3rd Forum for China–Africa University Presidents on Innovation and Development. He and Professor Song Xiaochun, President of Hubei University of Technology, signed a memorandum of understanding (MoU) between their two universities.

The MoU focuses on the following areas:

1. Launching joint master’s and PhD degree programs (MA and MSc/PhD).
2. Facilitating academic staff exchanges between the two universities.
3. Jointly organizing conferences and workshops.
4. Establishing joint research and scientific laboratories.
5. Cooperating on technological innovation and technology transfer.
6. Expanding cooperation to create entrepreneurship opportunities.
7. Working together under the China–Africa Belt and Road joint project framework.

Jinka University also signed a separate agreement with Hubei University of Technology, Addis Ababa Science and Technology University, and Jimma University to collaborate under the China–Africa Belt and Road joint project framework.