ነሃሴ 11/2017ዓ.ም
የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አሰፋ አስማረ በተገኙበት አዲስ የተመደቡት የአካዳሚክ፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ተጠባባቂ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተስፋዬ አለሙ እና የአስተዳደርና ልማት ተጠባባቂ ም/ፕሬዚዳንት ሆነው የተመደቡት ዶ/ር መልካሙ ዘሮ ከቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል።
በርክክብ ሂደቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ እንዲሁም የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባል አቶ አብርሃም አታ የተገኙ ሲሆን እስካሁን ድረስ ሲያገለግሉ የነበሩት አመራሮች ዩኒቨርሲቲው ላለበት ደረጃ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን በመግለፅ አዲስ የተመደቡት ተጠባባቂ ም/ፕሬዚዳንቶችም ጥሩ የስራ ከባቢን በመፍጠር በተባበረ ክንድ የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ ልያሳኩ የሚችሉ ለውጦችን ማምጣት እንደሚችሉ ተናግረዋል።
አዲስ ምደባ የተሰጣቸው ዶ/ር ተስፋዬና ዶ/ር መልካሙ ቦርዱ ለሰጣቸው ትልቅ ሀላፊነት በማመስገን በቅንነትና በታማኝነት ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ቁርጠኞች መሆናቸውን ገልፀው በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲው የተጀማመሩ አንዳንድ ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት የርክክብ ሂደቱ ተጠናቅቋል።









