መስከረም 30/2018ዓ.ም
ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ሊተገበሩ በታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች(KPIs)ዙሪያ የአፈጻጸም ውል ስምምነት ፊርማ ስነስርዓት አካሂዷል።
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገርና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርመዋል።
በዩኒቨርሲቲዎች እየተተገበረ የሚገኘው የተቋማት ልየታ(Differentiation) ትኩረት አድርገው ለመስራት የሚያስችላቸውን የትምህርት፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ታሳቢ ያደረጉ ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች(Key Performance Indicators) ተቆጥሮ የተሰጣቸው ሲሆን በቀጣይም በተሰጣቸው ተግባር ተለክተው የሚገመገሙ መሆኑንም ተገልጿል።
የፊርማ ስነስርዓቱ ዓላማ ተግባራትን ቆጥሮ ከመረካከብም ባለፈ ጥሩ ውጤት የሚያስመዘግቡ ሥራ አስፋጻሚዎች የበለጠ የሚበረታቱበት፤ ዝቅተኛ አፈጻጸም የሚያስመዘግቡት ደግሞ ተጠያቂ የሚሆኑበት ሥርዓትን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሆነም ተመላክቷል።


