jinka university ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር “የፋሲለደስ ስምምነትን” ለመተግበር የውል ስምምነት ተፈራረመ። – jinka university

Jinka University

Knowledge for Change.

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር “የፋሲለደስ ስምምነትን” ለመተግበር የውል ስምምነት ተፈራረመ።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር “የፋሲለደስ ስምምነትን” ለመተግበር የውል ስምምነት ተፈራረመ።

Posted By on 7/31/25 in News

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር “የፋሲለደስ ስምምነትን” ለመተግበር የውል ስምምነት ተፈራረመ።

**ሐምሌ 15/2017ዓ.ም**

“ማህበራዊ ትስስራችን ለአብሮነታችን” በሚል መሪ ቃል ጎንደር ዩኒቨርሲቲና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የቃልኪዳን ቤተሰብ ትስስርና ትውውቅ ሀገርአቀፍ የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም አካሂደዋል።

“የጎንደር የቃልኪዳን ቤተሰብ” ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከ2012ዓ.ም ጀምሮ በየአመቱ ወደ ዩኒቨርስቲው የሚገቡ ተማሪዎች በጎንደር ከተማ ውስጥ ከሚኖሩ ነዋሪዎች ተገቢውን ፍቅርና እንክብካቤ የሚያገኙበትና በቆይታቸው አስፈላጊውን ቤተሰባዊ ክትትልና ድጋፍ እንዲያገኙ ማስቻልን መሰረት ያደረገ ሀሳብ ነው።

ማህበረሰቡ ከተማሪዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመደቡ አዳዲስ ተማሪዎችን ከጎንደር ከተማ ማህበረሰብ ጋር በማስተሳሰር የቃልኪዳን ቤተሰብን በመፍጠር ተማሪዎች የእንግድነት ስሜት ሳይሰማቸው በትምህርትና ስልጠና ጊዜያቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ለማስቻል አላማ ያደረገ ሲሆን ሌሎች የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችም ከሚገኙባቸው የከተማ አስተዳደሮች ጋር በመተባበር ተግባራዊ እንዲያደርጉ የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ከጎንደር ዩኒቨርሲቲና ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሂደዋል።

በመርሃግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ሙሀመድ እንድሪስን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኢታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ፣ የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚደንቶች፣ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙባቸው ከተሞች ከንቲባዎችና የክልሎች የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክና የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ገልሺ ምንም እንኳን በጂንካ ከተማም በተወሰነ መልኩ በመተግበር ላይ የነበረ እንቅስቃሴ ቢሆንም በቀጣይ ልክ እንደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተቋማዊ በሆነ መልኩ አጠናክሮ ለመስራት “የፋሲለደስ ስምምነት” ተብሎ የተሰየመውን የቃልኪዳን ቤተሰብ ምስረታ ስምምነት ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ተፈራርመዋል።