jinka university ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ለሚገኙ የአቅም ውስንነት ላለባቸው ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። – jinka university

Jinka University

Knowledge for Change.

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ለሚገኙ የአቅም ውስንነት ላለባቸው ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ለሚገኙ የአቅም ውስንነት ላለባቸው ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

Posted By on 9/3/25 in Uncategorized

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ለሚገኙ የአቅም ውስንነት ላለባቸው ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ነሃሴ 14/2017ዓ.ም

በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አማካኝነት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ እና የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ አለሙ በተገኙበት ከአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ለተመረጡ ህፃናት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም መሠል የማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን በስፋት የሚሰራ መሆኑን ገልፀው በዚህ ዙር ለሁለቱ ዞኖች ከ5000 ደርዘን በላይ ደብተሮችን ዩኒቨርስቲው ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም ዩኒቨርሲቲው በተለይም በትምህርትና ሌሎች ትውልድን በመቅረጽ ሂደት ላይ በስፋት እንደሚሰራ የገለፁ ሲሆን የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ተስፋዬ አለሙ በበኩላቸው ከመማር ማስተማርና ምርምር ስራዎች ባሻገር የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች አንዱ የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ በመሆኑ በተጠናከረና ለውጥ ሊያመጡ በሚችሉ መልኩ እንደሚተገበር አብራርተዋል።

በመጨረሻም በትናንትናው ዕለት ማለትም ነሀሴ 13 ቀን 2017 ከአሪ ዞን ለተመረጡ ህፃና በተደረገው የድጋፍ ፕሮግራም የተገኙት የጂንካ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ውባለም ገዛኸኝ፤ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል በሚደረገው እንቅስቃሴ ለሚያበረከተው ድጋፍና ለተደረገው የትምህርት ቁሳቁስ አበርክቶ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።