jinka university በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ (IFMIS) ስርዐት ዝርጋታ የደረሰበትን አሁናዊ ሂደት ተገመገመ። – jinka university

Jinka University

Knowledge for Change.

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ (IFMIS) ስርዐት ዝርጋታ የደረሰበትን አሁናዊ ሂደት ተገመገመ።

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ (IFMIS) ስርዐት ዝርጋታ የደረሰበትን አሁናዊ ሂደት ተገመገመ።

Posted By on 7/31/25 in Uncategorized

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ (IFMIS) ስርዐት ዝርጋታ የደረሰበትን አሁናዊ ሂደት ተገመገመ።

******ሐምሌ 8/2017ዓ.ም******

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የፌዴራል ተቋማት በኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የሚተገበር የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር ስርዓት Integrated Financial Management Information System (IFMIS) የተባለ ሲስተም ተኮር የሆነ ስርዓት እየተዘረጋ ይገኛል።

ባለፈው ሚያዝያ 21/2017ዓ.ም ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ የስራ ሀላፊዎችና ለተለያዩ የስራ ክፍል ባለሙያዎች በሲስተሙ አጠቃቀምና ጠቀሜታ ዙሪያ ማብራሪያና ገለፃ መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ በተገኙበት “IFMIS”ን ወደ ተግባር ለማስገባት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትንና ቀሪ ስራዎችን በሚመለከት የአፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት ቀርቧል።

ሲስተሙን ለማስጀመር አብዛኛው ስራ ወደማጠናቀቅ መኬዱን ከገንዘብ ሚኒስቴር የመጡ የሲስተሙ ባለሙያዎች ገልፀው ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ለማስገባት በዋናነት ለፋይናንስ፣ ለንብረት አስተዳደር፣ ለግዢና ሌሎች ተዛማጅነት ላላቸው ስራ ክፍል ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በተከታታይነት ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።