jinka university የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄዱ። – jinka university

Jinka University

Knowledge for Change.

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄዱ።

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄዱ።

Posted By on 8/25/25 in News

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄዱ።

ነሃሴ 17/2017ዓ.ም

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክና የአስተዳደር ሰራተኞች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሂደዋል።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ዶ/ር ተስፋዬ አለሙ እንዲሁም የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር መልካሙ ዘሮ በተገኙበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የ2017 የክረምት በጎ አድራጎት ንቅናቄ በጂንካ ከተማ የፅዳት መርሃግብር በማካሄድ የተጀመረ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ አለሙ እንዲህ አይነት ተግባራት ዩኒቨርሲቲውን ከማህበረሰቡ ጋር የሚያስተሳስሩ ከመሆናቸውም ባሻገር ለጋራ ለውጥ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ወደፊትም መሠል የጽዳት ዘመቻና ሌሎች የበጎ አድራጎት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ከከተማ ፅዳት በተጨማሪ በቀጣይ ሌሎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚኖሩ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በፅዳት ዘመቻው የተገኙት የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሲሳይ ገልሺ በበኩላቸው የጽዳት ዘመቻው በአካባቢው የተንሰራፋውን የወባ በሽታን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ ዩኒቨርሲቲው ወደ ማህበረሰቡ በመግባት የሚያከናውናቸው የልማትና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ሌሎችንም የሚያነሳሳ መሆኑን ተናግረው ተሳታፊዎችን አመስግነዋል።