jinka university እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት በዓል አደረሰን። – jinka university

Jinka University

Knowledge for Change.

እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት በዓል አደረሰን።

እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት በዓል አደረሰን።

Posted By on 10/29/25 in News

እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት በዓል አደረሰን።

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ ያለን!!

#ከግድብም በላይ- አባይ!!

እንኳን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት በዓል አደረሰን።
=======

በህብረት የመቆም ተምሳሌት፣ የአላማ ፅናትና በተግዳሮቶች ያለመሸነፍ ውጤት እንዲሁም ለሉዓላዊነትና በራስ አቅም የማድረግ ማሳያ። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ።

ጳጉሜ 4/2017ዓም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የታላቅ ስኬት የማብሰሪያ ዕለት ነውና እንኳን ደስ አለን። ብዙ ቤቶች በብርሃን የሚደምቁበት፣ ዘርፈብዙ የዲፕሎማሲ ጫናወች የሚቃለሉበት፣ የሚልዮኖች ላብ፣ ደምና የገንዘብ ጥሪት ፍሬ ያፈራበት ስለሆነ ከግድብም በላይ ነው።

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብም እንደሁሉም ኢትዮጵያዊ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ በቦንድ ግዢ ተሳታፊ ከመሆንም በላይ በ2015ዓ.ም በመንግሥት ተቋማት ደረጃ ከተፈፀሙ የቦንድ ግዢዎች መካከል ከፍተኛውን ደረጃ በመያዝ ከማስተባበሪያ ፅ/ቤቱ የምስጋናና የእውቅና የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው መሆኑን አይዘነጋም።

ይህንን ታላቅ የስኬት መነሻ ላስጀመሩት፣ ላስቀጠሉትና ላጠናቀቁት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ክብር ይገባቸዋል በትውልድ ሁሉም ሲዘከሩ ይኖራሉ። እናመሠግናለን!!

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በድጋሚ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ስም እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!

ዶ/ር ዮሐንስ ይትባረክ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት!!