Regular teaching learning process for graduating students is according to the admission program

It is to be recalled that the teaching and learning process has been disrupted more than any other cause due to the CVD-19 epidemic in our country and the world. However, in line with the government’s direction to continue the teaching and learning process of the CVD-19 virus in our country, Jinka University graduates from November 21, 2013 E.C. The president of the university, Dr. Kusse Gudishe, who is currently teaching, said that out of the 874 students who should have graduated from the university, 870 are currently attending school and are expected to graduate on January 26, 2013 E.C.
Eighty percent of our graduates, according to the Science and Higher Education program, are expected to return to their former university in 2012 due to the CVD-19 epidemic, and those who have already entered the university should stay there, and those on the road should stay close to them and stay with their families. Dr. Alemu Hailete, Vice President of Administration and Student Services of the University, said that the university has provided training for the students on dormitories and cafes as well as the CVD-19 virus protocol until November 30, 2013 E.C.
According to Dr. Mohamed, Director of the University’s Pre-Graduation and Postgraduate Program Directorate, the university has about 230 teachers, not to mention the newly hired faculty members.
According to the Ministry of Science and Higher Education’s plan to enter our university on October 25 and 26, 2013 E.C, we have been providing food and dormitory services to the university for at least a month due to the TPLF’s brutal attack on our North Command in the Tigray region. The students who commented that the junta also got their hands on it and that we were excited to start studying at the university and that we are now looking forward to our graduation day.

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በመልሶ ቅበላ መርሃ ግብር መሰረት የተቀበላቸዉን ተመራቂ ተማሪዎች በጥሩ ሁኔታ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ አሰታወቀ
በመላ ሀገራችንና በዓለም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከዬትኞቹም ተግባራት በላይ የመማር ማስተማር ሂደት መስተጓጎሉ የሚታወስ ነው፡፡ይሁን እንጂ በሀገራችን የኮቪድ-19 ቫይረስ ስርጭትን በተገቢዉ ጥንቃቄ እየተከላከልን የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቀጥል መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የጂንካ ዩኒቨርሲቲም ተመራቂ ተማሪዎቹን ከህዳር 21/2013 ዓ/ም ጀምሮ በማስተማር ላይ ይገኛል ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ በዩኒቨርሲቲው መመረቅ ከነበረባቸው 874 ተማሪዎች መካከል አሁን ላይ 870 የሚሆኑት ትምህርታቸዉን በጥሩ ሁኔታ እየተከታተሉ እንደሚገኙና ጥር 15/2013 ዓ/ም ይመረቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል፡፡
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ2012 ዓ/ም ሳይመረቁ የቀሩት ተማሪዎች ወደ ነበሩበት ዩኒቨርሲቲ እንዲመለሱ የሳይንስነና ከፍተኛ ትምህርት ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት ቀድመው ወደ ዩኒቨርሲቲያቸው የገቡትን እዛው እንዲቆዩ፣በመንገድ ላይ የሚገኙትም ወደ ሚቀርባቸዉ እንዲሄዱና ጉዞ ያልጀመሩትም ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቆዩ መንግስት መግለጫ በሰጠበት ወቅት ከተመራቂ ተማሪዎቻችን መካከል ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ገብተው እንደነበር ያስታወሱት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አለሙ ሀይለቴ ዩኒቨርሲቲው ለእነዚሁ ተማሪዎች የመኝታና የካፌ አገልግሎት እንዲሁም በኮቪድ-19 ቫይረስ ፕሮቶኮል ዙሪያ ስልጠና በመስጠት እስከ ህዳር 20/2013 ዓ/ም ማቆየቱንም ተናግረዋል፡፡
ከተመራቂ ተማሪዎቻችን መልሶ ቅበላ ቀደም ብሎ የዩኒቨርሲቲው መምህራን በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰው በቂ ዝግጅት አንዲያደርጉ ተደርጓል ያሉት የዩኒቨርሲቲው የቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ኮማንደር መሃመድ ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ አዲስ የቀጠራቸዉን መምህራን ሳይጨምር ወደ 230 መምህራን እንዳሉትም ገልፀዋል፡፡
ጥቅምት 25 እና 26/2013 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲያችን እንድንገባ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት ወደ ዩኒቨርሲቲው ብንደርስም በትግራይ ክልል በሰሜን እዝ መከላኪያ ኃይላችን ላይ ጁንታው የህወሃት ሀይል በፈፀመው አረመኔያዊ ጥቃት ምክንያት ከ1 ወር ለማያንስ ጊዜ ያለትምህርት ዩኒቭርሲቲው የምግብና የመኝታ አገልግሎት እየሰጠን ቆይተናል ያሉት አንዳንድ አስተያየታቸዉን የሰጡን ተማሪዎች ጁንታዉም የእጁን አግኝቶ እኛም ዩኒቨርሲቲው ባደረገው በቂ ዝግጅት መማር መጀመራችን በጣም ያስደሰተን ሲሆን አሁን ላይ እንድንመረቅ የተቆረጠልንን ቀን በናፍቆት አየተጠባበቅን እንገኛለን ብለዋል፡፡