በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እድል ተሰጥቷቸው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ እንደሆነ ገለፁ።

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እድል ተሰጥቷቸው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ እንደሆነ ገለፁ።

*ጥር 27/2014*

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ የጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ጥሩ የቆይታ ጊዜ እያሳለፍን ነው ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

ሀገራት የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ለውጭ ሀገር ዜጎች የትምህርት እድል መስጠት ከብዙ የዲፕሎማሲያዊ መስተጋብሮች መካከል አንዱ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያም ከሌሎች ሀገራት ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አንድ እርምጃ ከፍ ለማድረግ በተለይም ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የምትገኝበትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማሻሻል የሀገሪቱን የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አለማቀፋዊ የማድረግ እስትራቴጂዎችን በመንደፍ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች።

ስለሆነም ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ የሆነው ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት አስራ ሰባት የደቡብ ሱዳን ዜጎችን ተቀብሎ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ይህንን ሀገራዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫና አለማቀፋዊነትን ለመደገፍ ዩኒቨርሲቲው ከነደፈው የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድ ውስጥ ለውጭ ሀገር ዜጎች የነፃ ትምህርት ዕድል መስጠትን እንደ አንድ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝበት አካባቢ (ደቡብ ኦሞ ዞን) ድንበር አካባቢ በመሆኑ ከጎረቤት ሀገራት ቀጠናዊ ትስስር ለመፍጠር ምቹ ሁኔታዎች ስላሉ ይህንን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ለሀገራችን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅበት የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ያምናሉ።

ይህንን እቅድ ለማሳካት በዘንድሮው አመት ብቻ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የነፃ ትምህርት ዕድል ያገኙ አስራ ሰባት ያህል ደቡብ ሱዳናውያን ይገኛሉ።

የእድሉ ተጠቃሚ ለሆኑት ተማሪዎች እንዳጠቃላይ የኢትዮጵያ ቆይታቸው በዋናነት ደግሞ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ላይ እያሳለፉት ስላለው የትምህርት ጊዜ በተደረገላቸው ቃለመጠይቅ መሰረት ሀሳባቸውን እንደሚከተለው ገልፀዋል:-

“ጋች እባላለሁ የመጣሁት ከደቡብ ሱዳን ነው። የኢኮኖሚክስ ሁለተኛ አመት ተማሪ ነኝ። የኢትዮጵያ ቆይታዬ አሁን ሰባት ወር አካባቢ ነው። ኢትዮጵያ ላይ ትምህታቸውን ከሚከታተሉ የውጭ ሀገር ዜጎች መካከል አንዱ ነኝ። ኢትዮጵያ በጣም ጥሩ ሀገር ነች። ብዙም የእንግዳነት ስሜት ሳይሰማን ትምህርታችንን እየተከታተልን እንገኛለን።”

“ስሜ ዲንግ የን ነው። እዚህ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በመማር ላይ ካለን አስራ ሰባት ያህል ተማሪዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ። አሁን የሁለተኛ አመት ተማሪ ስሆን የአካውንቲንግ ትምህርት እያጠናሁ ነው። የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በጣም አዎንታዊ ነው። ሀገርህ ላይ ያለህ እስኪመስልህ ድረስ ነው ቤተሰባዊ ፍቅር የሚሰጥህ። ለነገሩ እኛም እንደሁለተኛ ሀገራችን ነው የምንቆጥራት ኢትዮጵያን። ምክንያቱም እኛጋም ቢሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችን በንግዱም ሆነ በሌሎች የስራ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው እየኖሩ ይገኛሉ። እዚህ ጋምቤላ ላይም ብዙ ሱዳናውያን አሉ ለዚህም ነው እንደ ሁለተኛ ሀገራችን የሚሰማን”

“የአየር ሁኔታው ተመሳሳይነት፣ የህዝቡ ቅንነትና የአኗኗር ዘይቤው በጣም ደስተኛ ያደርጋል። አንዳንድ ጊዜ በቆይታችን በቋንቋ ምክንያት የመቸገር ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም። በተለይ አንዳንድ ጊዜ ክፍል ውስጥም ቢሆን ይህ ችግር ይገጥመን ነበር ነገር ግን ለመምህራኖቻችን በማሳወቅ በእንግሊዝኛ ብቻ በመግባባት የቋንቋ ችግራችንን ይቀርፉልናል።”

#########################

Students from South Sudan, who are studying at Jinka University, mentioned as they are spending a good time.

*4th of Februar /2022*

Providing education to foreigners to strengthen countries tie is one of the many diplomatic interaction systems.

Ethiopia is also working to enhance its diplomatic relations with other countries by providing scholarships to foreign country citizens. This helps to internationalize the higher education institutions of the country, too.

As a result, Jinka University, one of the government’s higher education institutions, received 17 students who have got scholarship chance with UN from South Sudan to achieve this national vision.

In support of this national diplomatic strategy, the university has set out its ten-years strategic plan to provide scholarships to foreigners especially neighbor countries.

Jinka University is located at south omo zone near the border part of Ethiopia. Hence, JKU has provided scholarship to 17 South Sudanese students just this year.
According to South Sudanese students who have took advantage of the opportunity, their stay in Ethiopia in general, and in particular at Jinka University, is very well. Here under is the word of some of them:

“My name is Gach and I am from South Sudan. I am second year Economics student. I have been in Ethiopia for about seven months now. I am one of the foreigners studying in Ethiopia. Ethiopia is a very good country. We are studying without feeling loneliness.”

“My name is Deng. I am one of the seventeen students who are studying at Jinka University. I am studying Accounting. The university community is very positive. They are giving us familyhood love . Therefore, we are feeling as we are in our country. By the way, we consider Ethiopia as our second home. Because many of our Ethiopian brothers are engaged in different business activities in South Sudan. There are many Sudanese here in Gambella, too. That is why we are thinking Ethiopia as our second home.”