If we can bring AI (Artificial Intelligence) to our university, it will be the biggest revolution

“አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስን በዩኒቨርሲቲያችን ማስገባት ከቻልን ትልቁ አብዮት ይሆናል” ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ፣ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

https://www.ethiopianreporter.com/article/19680
ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ናቸው። ተወልደው ያደጉት ደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ ሜፀር በምትባል አነስተኛ ቀበሌ ነው። ባደጉባት ሜፀር ቀበሌ ሁሉንም የክፍል ደረጃ የያዘ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ምክንያት ትምህርታቸውን የተከታተሉት በከባድ ችግር ነው። ከክፍል ወደ ክፍል ባለፉ ቁጥር በትምህርት ቤት እጥረት ምክንያት ከከተማ ከተማ በመቀያየር ትምህርታቸውን ተከታተሉ። የደረጃ ተማሪም ነበሩ። በዚህ ሁኔታ የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሺዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በሶሻል አንትሮፖሎጂ የማስተርስ ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ውጤት ያዙ። ፒኤችዲያቸውን ከአሜሪካ ፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ በሶሻል አንትሮፖሎጂ፣ ድኅረ ዶክትሬታቸውንም ደግሞ በጃፓን ሠርተው ወደ አገራቸው በመመለስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሻል አንትሮፖሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ በመሆን አስተምረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በመሆንም አገልግለዋል። በአሁኑ ጊዜ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ናቸው። በጂንካ ዩኒቨርሲቲና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ናርዶስ ፍቃዱ አነጋግራቸዋለች።
ሪፖርተር፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ነው የተቋቋመው? በየትኞቹ መስኮች ትምህርትን ተደራሽ ታደርጋላችሁ?
ፕሮፌሰር ገብሬ፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመው በ2010 ዓ.ም. ነው። በ2013 ዓ.ም. ለአራተኛ ጊዜ ተማሪዎችን ይቀበላል። የመጀመሪያው ዙር ተማሪዎቻችን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት ባይቋረጥ ኖሮ ይመረቁ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲው አራት ኮሌጆችና 14 ዲፓርትመንቶች አሉት። አራቱ ኮሌጆች የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ፣ ማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም የግብርና ሳይንስ ናቸው። የተፈጥሮ ሳይንስና የግብርና ሳይንስ ኮሌጆች እያንዳንዳቸው አራት ዲፓርትመንቶች አሏቸው። የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ እያንዳንዳቸው ሦስት ዲፓርትመንቶች አሏቸው፡፡ በ2013 ዓ.ም. አሥር ዲፓርትመንቶችን ለመጨመር ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን። ይህ የዲፓርትመንት ቁጥሩን ወደ 24 ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪም አራት የማስተርስ መርሐ ግብሮችን ለመጨመር ዝግጅት ላይ ነን።
ሪፖርተር፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እንዲመጡ የተደረገበት ምክንያት ምንድን ነው?
ፕሮፌሰር ገብሬ፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እንድመጣ የተደረገበት አንዱና ትልቁ ምክንያት የዚህ አካባቢ ልጅ ስለሆንኩና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለመሆን ብቃት አለው ብለው ስላመኑ ነው። ነገር ግን ጥያቄው ሲቀርብልኝ የቤተሰብ ጉዳይ ስለነበረብኝ በሌላ መንገድ ነበር ለመርዳት የወሰንኩት። ስምምነታችንም የነበረው የቦርድ አባል ሆኜ ለማገልገል ነበር። ነገር ግን ለቦታው የምትመጥን ሰው ነህ በማለትና አሳማኝ ነጥቦችን በማስቀመጥ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብልኝ ለመሞከር ወሰንኩ። ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ በፕሬዚዳንትነት እያገለገልኩ እገኛለሁ።
ሪፖርተር፡- ዩኒቨርሲቲው ስንት ተማሪዎችን ይዟል? ለስንት ሰዎችስ የሥራ ዕድል ፈጠረ? በቀጣይስ የቅበላ አቅሙን በማሳደግ ዙሪያ ምን አስቧል?
ፕሮፌሰር ገብሬ፡- የተማሪዎች ቁጥር በሦስት ዙር ቅበላ የክረምትና የቅዳሜ፣ እሑድን ጨምሮ 4400 ደርሷል። ከሥራ ዕድል አንፃር በቋሚነት ከ200 በላይ መምህራንና 700 ያህል የአስተዳደር ሠራተኞች አሉ። ከዛ ውጪ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመከፈቱ ጀምሮ ከግንባታ በመነሳት በርካታ ማኅበራት ተጠቃሚ ሆነዋል። ለ2013 ዓ.ም. 3000 ያህል ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅታችንን አጠናቀናል።
ሪፖርተር፡- የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ዓላማዎች ምንድን ናቸው? እስካሁንስ ምን ምን ነገሮችን አከናውኗል?
ፕሮፌሰር ገብሬ፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት። የመጀመርያው መማር ማስተማር፣ ሁለተኛው ምርምርና የመጨረሻው የማኅበረሰብ አገልግሎት ነው። በመማር ማስተማሩ ዙርያ መጀመሪያ ዓመት ላይ ማለትም በ2010 ዓ.ም. 1500 ተማሪ ጠብቀን የመጣልን ግን 1099 ተማሪ ነው። ቅበላውን የጀመርነው በጥር ወር ላይ በመሆኑ ተማሪዎች ሌሎች አማራጮችን ወስደዋል። የተቀሩት ተማሪዎችም ለዩኒቨርሲቲው የመጀመርያ ተማሪዎች በመሆናቸው አርባ ምንጭ ድረስ ሄደን ነበር የተቀበልናቸው። የማኅበረሰቡም አቀባበል ደማቅ ነበር። በመቀጠልም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ምደባ ድረስ ያለውን ሒደት ቀላል አድርገናል። እንዲሁም የዲጂታል ላይብረሪ ሥርዓት በመጠቀም ኢንተርኔት የማይፈልግ ስልክን ወይም ኮምፒዩተርን በመጠቀም ተማሪዎች በቀላሉ መጽሐፍ የሚያገኙበትን ዕድል አመቻችተናል። ከዚሁ ከመማር ማስተማር ሒደት ሳንወጣ ለመምህራን ተጨማሪ ሥልጠናዎችንና ለተማሪዎችም አጋዥ ትምህርቶችን በመስጠት ተማሪዎችን በመደገፍ የመባረር ምጣኔውን ለመቀነስ ችለናል። የዩኒቨርሲቲያችን ሁለተኛው ዓላማ ምርምር ነው። በመጀመሪያ ዓመት መንግሥት ብር ባለመመደቡ ምክንያት ምርምር መሥራት አልቻልንም ነበር። ነገር ግን በሁለተኛው ዓመት ገንዘብ ማግኘት በመቻላችን ሠላሳ አምስት ፕሮፖዛል ቀርቦ ሠላሳው በማለፋቸው ገንዘብ መድበንላቸው ጥናት አድርገው የጥናቱን ውጤት ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርት መልክ ያቀረቡትንም እንዲያሳትሙ እየተሞከረ ነው። ሦስተኛ ዓመት ላይም እንዲሁ 67 ፕሮፖዛሎች ቀርበው 47 ተመርጦ ጥናታቸውን በጀመሩበት ወቅት ነው በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠው። ሌላው በምርምር ሥራ የሠራነው የተለያዩ ኮንፍረንሶችን ማዘጋጀት ነው። ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከሌላው ዩኒቨርሲቲ ለየት ባለ መልኩ ትምህርት መስጠት ሳንጀምር በፊት ነው፣ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችን ማዘጋጀት የጀመርነው። እስካሁንም በብዝኃ ሕግጋትና ሥርዓተ ፆታ ላይ ያጠነጠኑ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንሶችንና ሦስት የአገር ውስጥ ኮንፍረንሶችን አዘጋጅተናል።
ሦስተኛው የዩኒቨርሲቲያችን ዓላማ የማኅበረሰብ አገልግሎት ነው። በዚህ ውስጥም በርካታ ሥራዎችን ሠርተናል። በመጀመርያ ትኩረት ያደረግነው ትምህርት ላይ ነው። ምን ችግር አለ ብለን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጀምረን በጠየቅን ጊዜ የመጽሐፍ እጥረትና የኮምፒዩተር አለመኖርን በመገንዘባችን ችግሩን ለመቅረፍ ከካማራ ኤድዩኬሽን ኢትዮጵያ ጋር በመነጋገር ወደ 700 ኮምፒዩተሮችን በመግዛትና ኮምፒዩተሮች ላይ መጻሕፍትን በመጫን ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሥልጠና ሰጥተን አድለናልን። እነዚህ ኮምፒዩተሮች የታደሉት የጂንካ ማረሚያ ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጨምሮ ለሠላሳ አራት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና ለአንድ ሞዴል ማድረግ ለፈለግነው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። ይህም በትንሹም ቢሆን ከሌሎች የኢትዮጵያ ተማሪዎች ጋር ለመወዳደር ያስችላቸዋል ብለን እናስባለን። ሌላው ለሦስት አቅመ ደካማ እናትና አባቶች ከተማሪው ጋር በመሆንና ገንዘብ በማዋጣት ቤት ሠርተን ሰጥተናል። ይኼ በእርግጥ የሚያኩራራ ሥራ ባይሆንም በቀጣይ ግን መነሳሻ የሚሆን ነው ብለን እናምናለን። በተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ላይም እንዲሁ እየተሳተፍን እንገኛለን። ለምሳሌ ያህል በተወሰነ መልኩ እየተራቆተ የሚገኘውን ከጂንካ ከተማ አጠገብ ባለው የጎሪጎቻ ተራራ ላይ ማኅበረሰቡን በማሳተፍ ችግኝ በመትከል ጥበቃ እንዲደረግለት አድርገናል። ለመንግሥት ሠራተኞች አቅም ማጎልበቻ የተለያዩ ሥልጠናዎችንም ሰጥተናል። ከዚህ በተጨማሪ የደቡብ ኦሞ ባህል ፌስቲቫልም ጀምረናል። ለዘንድሮ በኮቪድ-19 ምክንያት ሳይሳካ የቀረው የዚህ ፌስቲቫል ዓላማ በደቡብ ኦሞ ያሉ 16 ብሔረሰቦች ቱባ የሙዚቃ፣ የምግብ እንዲሁም የዕደ ጥበብ ባህል ስላላቸው እሱን ለተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ማስተዋወቅና የገቢ ምንጭ ማምጣት ነው። በዚህም መሠረት የመጀመርያው ዙር በጥሩ ሁኔታ ተካሄዷል። ሌላው የኮሮና ቫይረስ በአገሪቱ ከተከሰተ በኋላ ዩኒቨርሲቲው ከክልሉ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ጋር በመተባበር ሳኒታይዘር በማምረት በመጀመርያ ዙር ለተወሰነ ማኅበረሰብ ክፍል በነፃ ካደልን በኋላ በቀጣይ ያለ ትርፍ በተመጣጣኝ ዋጋ እያመረትን ማከፋፈል ጀምረናል። በዚህም ባለማቆም ወደ አምስት ሚሊዮን ብር በማውጣት የኮሮና ቫይረስ መመርመርያ ማሽኖችን በመግዛትና ለሱ የሚሆኑ ግንባታዎችን በማከናወን ምርመራ ለማድረግ እየተዘጋጀን እንገኛለን። ይኼንና የመሳሰሉት በማኅበረሰብ ዙርያ ዩኒቨርሲቲው የሠራቸው ሥራዎች ናቸው።
ሪፖርተር፡- በመላ ኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት የፀጥታ ችግር በሰፊው ተስተውሏል። የዚህ ችግር ሰለባዎችም በተቀዳሚነት ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በእነዚህ ጊዜያት ምን ዓይነት ችግሮች አጋጠሙት? እንዴትስ ተወጣው?
ፕሮፌሰር ገብሬ፡- እውነት ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም በለውጡ ጊዜ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ችግር ላይ ነበሩ። የእኛ ዩኒቨርሲቲ ሁለቱን ዓመት ያለ ምንም ኮሽታ አሳልፈናል። ሦስተኛ ዓመት ላይ ግን የተወሰኑ ተማሪዎች ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ተደራጅተው ነበር የመጡት። አስቀድሞ መረጃ ደርሶን ስለነበረ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርገናል። አንድ ቀን ብቻ አርባ የሚጠጉ ተማሪዎች በመመገቢያ ካፌ ውስጥ ምግብ አንስቶ ያለመብላትና ባነሱት ምግብ ላይ ውኃ የመጨመር አድማ በማድረግ ችግር ለማስነሳት ሞክረዋል። በዩኒቨርሲቲያችን ትልቁ የደረሰው ክስተት የምንለው ይህንን ነው። ለእነዚህ ተማሪዎች የምክር አገልግሎት ሰጥተናል። ከእነዚህም ውስጥ አሥራ ሁለት የሚጠጉ ተማሪዎች የአንድና የሁለት ዓመት ዕገዳ እንዲሁም የማስጠንቀቂያ ቅጣት ተወስዶባቸዋል።
ሪፖርተር፡- ኮሮና በኢትዮጵያ ከተከሰተ በኋላ ከተወሰዱ ዕርምጃዎች መካከል አንዱ ዩኒቨርሲቲዎችን መዝጋትና ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ማድረግ ነበር። ተማሪዎቻችሁ ወደቤት ከላካችሁ በኋላ ግንኙነታችሁ ምን ይመስላል?
ፕሮፌሰር ገብሬ፡- ተማሪዎች ወደየቤታቸው መሄድ አለባቸው የሚል መመርያ እንደተሰጠ ወዲያው ተማሪዎችን ወደ ቤታቸው ለመላክ ወሰንን። ነገር ግን ከቤተሰብ ወዲያው ብር አስልከው መሄድ ትንሽ አስቸጋሪ ነበር። በጣም ጥቂት ተማሪዎች በግላቸው ሄዱ። ነገር ግን አብዛኛው ተማሪ መሄድ ስላልቻለ ሰማንያ አውቶቡሶችን በማዘጋጀት ዩኒቨርሲቲው እንዲያደርሳቸው አድርገናል። በአሁኑ ወቅት የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች በበሽታው ምክንያት ቤታቸው ሲሆኑ፣ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተሟላ ግንኙነት ኖሯቸው በኦንላይን ትምህርት እያገኙ አይደለም። በኦንላይን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙት የማስተርስና የፒኤችዲ ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
ሪፖርተር፡- ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለቀጣይ ምን አስቧል?
ፕሮፌሰር ገብሬ– የመጀመርያው ያለንን አጠናክሮና አሻሽሎ መሄድ ነው። ይህም በላይብረሪ፣ በሬጅስትራር እንዲሁም በመማር ማስተማር የምንሰጠውን አገልግሎት አጠናክረንና አዘምነን መሄድ ነው። ሁለተኛው የቴክኖሎጂውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ ነው። ለምሳሌ አሜሪካ ካለ አንድ ተቋም ጋር በመተባበር ለአሥራ አንድ ዩኒቨርሲቲዎች የአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ለማስገባት ዕቅድ አለ። ከአሥራ አንዱ ዩኒቨርሲቲዎች መካከልም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው። ስለዚህ አርቴፊሺያል ኢንተለጀንስን በዩኒቨርሲቲያችን ማስገባት ከቻልን በጣም ትልቁ አብዮት ነው የሚሆነው። ከዚህ በተጨማሪም አምስት የሚሆኑ የልህቀት ማዕከላት አሉ። ሁሉም ላይ ባይሆንም የተወሰኑት ላይ መሥራት እንፈልጋለን። አካባቢያችን አርብቶ አደር የበዛበት፣ የእንስሳት ሀብት በብዛት ያለበት በመሆኑ እዛ ላይ መሥራት እንፈልጋለን። ይኼም በእንስሳት ሀብት ዙርያ ለአገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ሌላው እንደ ልህቀት ማዕከል ማየት የምንፈልገው ዞኑ የአሥራ ስድስት ብሔረሰቦች ስብስብ እስከሆነ መጠን ሕብረ ብሔራዊነት ላይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የልህቀት ማዕከል ይሆናሉ ብለን የምናስባቸው አራቱ የስኳር ፋብሪካዎች ናቸው። ሌላው ደግሞ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በደቡብ ኦሞ በመገኘቱና ደቡብ ኦሞ ከኬንያና ከደቡብ ሱዳን ጋር በመጎራበቱ አኅጉራዊ ቀጣናዊ ግንኙነትን ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከኬንያ ሕዝቦች ጋር እንዲሁም ከደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት እንዲጎለብት ያደርጋል የሚል እምነት አለን። ይኼ ሁሉም ዩኒቨርሲቲ የማይታደለው ለእኛ በጓሮአችን ያለ ዕድል ስለሆነ ከዚህ በላይ ልንሠራ አስበናል።

Jinka University in the Reporter
*******************************
“If we can bring artificial intelligence to our university, it will be the biggest revolution,” said Professor Gebre Yintiso, President of Jinka University.
According to the newspaper Reporter
Professor Gebre Yintiso is the President of Jinka University. He was born and raised in South Omo Zone, South Ari Woreda, and a small kebele called Metser. Due to the lack of an all-grade school in Metser Kebele, where they grew up, they attended school with serious difficulty. Each time they moved from class to class, they moved from city to city to attend school. He was also a high school student. After completing his 12th grade education, he earned a bachelor’s degree in sociology from Addis Ababa University and a master’s degree in social anthropology. He completed his PhD in Social Anthropology from the University of Florida in the United States and returned to his home country to teach at the Department of Social Anthropology at Addis Ababa University. He also served as dean of the College of Social Sciences at Addis Ababa University. He is currently the President of Jinka University. Nardos spoke to them about Jinka University and related issues.
The Reporter: Jinka University was recently established? In what areas do you make education accessible?
Prof. Gebre – Jinka University was established in 2010 E.C is it 2013 E.C Admits students for the fourth time. In the first round, our students would have graduated if they had not dropped out of school due to the CV-19 epidemic. The university currently has four colleges and 14 departments. The four colleges are natural and mathematical sciences, social sciences, business and economics, and agricultural sciences. The College of Natural Sciences and Agricultural Sciences each has four departments. The other two have three departments each. 2013 We are preparing to add ten departments. This is expected to increase the department’s number to 24. We are also planning to add four master’s programs.
The Reporter: Why did you come to Jinka University?
Professor Gebre – Jinka: One of the main reasons I came to the university was because I was a local and I believed he was qualified to be president of the university. But when I was asked, I had a family issue, so I decided to help in some other way. Our agreement was to serve as a board member. But I decided that what I really needed to do was learn how to do it right. So I have been serving as president since the university was founded.
How many students does the university have? How many jobs did he create? What does he think next about increasing his admission capacity?
Prof. Gebre: The number of students has reached 4,400 in three rounds of enrollment, summer and Saturday, including Sunday. In terms of job opportunities, there are more than 200 permanent teachers and about 700 administrative staff. In addition, since the opening of Jinka University, many associations have benefited from the construction. For 2013 We are ready to accept 3,000 students.
What are the goals of Jinka University? What has he accomplished so far?
Prof. Gebre – Jinka University, like other universities, has three main objectives. The first is learning, the second is research and the last is community service. In the first year of teaching and learning, in 2010. We have 1,500 students, but 1099 students. Since we started enrolling in January, students have taken other options. The rest of the students were the first students of the university, so we went to Arba Minch and welcomed them. The community was welcoming. Next, we simplified the process from registration to placement using technology. We have also made it possible for students to easily access books using a digital library system that does not require Internet access. Without further ado, we have been able to reduce the expulsion rate by supporting students by providing additional training and tutoring for teachers. The second purpose of our university is research. In the first year, we could not do research because the government did not allocate money. However, in the second year, we were able to raise funds, and thirty-five proposals were put forward, and thirty-more funds were allocated, and they conducted a study and reported on the results of the study. Attempts are also being made to publish your report. In the third year, 67 proposals were submitted and 47 were discontinued due to Covid-19. Another thing we did in research was to organize various conferences. Before we started teaching Jinka University in a different way, we started organizing international conferences. So far, we have organized international conferences on pluralism and gender, and three domestic conferences.
The third purpose of our university is community service. In this we have done a lot of work. Our focus is on education. When we asked what was wrong with the high school, we realized that there was a shortage of books and a lack of computers. These computers were donated to thirty-four high schools, including Jinka Prison High School, and to one model school. We think this will enable them to compete at least with other Ethiopian students. We also built a home for three disabled mothers and fathers, along with the student and donating money. This is certainly not a proud project, but we believe it will be an inspiration in the future. We are also involved in the conservation of natural resources. For example, we involved the community by planting seedlings on Mount Gorigocha, near the town of Jinka, which was partially degraded. We have also provided various trainings for civil servants capacity building. We have also started the South Omo Cultural Festival. The purpose of this festival, which has failed this year due to Covidy-19, is to promote and generate revenue for the rest of Ethiopia, as the 16 ethnic groups in South Omo have a rich culture of music, food and crafts. Accordingly, the first round went well. Following the outbreak of the cholera virus in the country, the university, in collaboration with the regional health institute laboratory, produced a sanitizer and distributed it to a section of the community free of charge in the first round. With this in mind, we are preparing to spend about five million birr to purchase corona virus scanning machines and to build constructions for it. This and the like are the work of the university around the community.
The Reporter: There has been widespread insecurity throughout Ethiopia, especially in the last two years. Universities are also the main victims. What problems did Jinka University face during these times? How did he do it?
Professor Gebre: That’s right. During the last two years, many universities have been in trouble. We spent two years at our university without a hitch. In the third year, however, some students were assigned and organized.