ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለ2012 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ደማቅ የእንኳን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም አዘጋጀ። በዝግጅቱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ የመንግስት አመራር አካላት፣ የማህበረሰብ ተወካዮችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ ደቡብ ኦሞ (ትንሿ ኢትዮጵያ) የሰላምና የፍቅር መንደር ስለሆነች ተማሪዎች ያለምንም ስጋት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና ምንጊዜም ከጎናቸው እንደማይለዩ አረጋግጠዋል። የደቡብ ኦሞ ዞን ባህል ክነት ቡድንና ሐበሻ ኢንተርተይንመንት ቡድን ፕሮግራሙን በአዝናኝ ዝግጅት ያደመቁ ሲሆን ታዳሚዎች የምሳ ግብዣ ከተደረገላቸው በሗላ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
ዕውቀት ለለውጥ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ