One-week awareness training was given to the university’s financial professionals in IBEX System

Opening the training, Dr. Alemu Aylate, Vice President of the University Administration and Student Services, said such training provided by senior professionals and it will be not only make the financial system of the institution more efficient and effective. Director, Finance Directorate Mrs. Almaz Alemu, for his part, urged the trainee not only to be trained but also to follow up on the training in practically the financial flows in IBEX System. Yonas Abebe, a senior expert at the Ministry of Finance’s Government Accounting Directorate, said the training will be effective and should be managed in a coordinated and efficient manner. Dereje Mekonnen, head of the Financial Management and Ibex Implementation Team at the Ministry of Finance, on his part, said that during the implementation of Ibex, it is important to properly record the necessary expenditure and accounting information and to avoid internal audits in purchasing and asset expenditure.
The training was given with presentations, coffee discussion and Ibex implementation, during which the participants and the trainers exchanged various comments, questions

በፋይናንስ አሰራርና በአይቤክስ /IBEX System/ ትግበራ ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ፋይንስ ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የአንድ ሳምንት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎሎ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓለሙ አይለቴ እንደገለጹት በተገቢው በከፍተኛ ባለሙያዎች የሚሰጥ የዚህ ዓይነት ስልጠና የተቋሙን የፋይናንስ አሰራር ቀልጣፋና ዉጤታማ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር የዳይሬክቶሬቱ አሰራር ሪፎርም ለማድረግ የላቀ ሚና ስለሚኖረው ሰልጣኞች በንቃትና በተነሳሽነት ስልጠናዉን ተከታትለው እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዲሬክተር ወ/ሮ አልማዝ ዓለሙ በበኩላቸው ሰልጣኙ ሰልጥኗል ብቻ ሳይሆን ከስልጠናው በኋላ በአግባቡ ተግብሯል እንዲባል ስልጠናዉን በአግባቡ እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡ የምንሰጠዉን ስልጠና ዉጤታማ መሆኑን ለማረጋገጥ ክትትልና ድጋፍ እናደርጋለን ያሉት በገንዘብ ሚነስቴር የመንግስት ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዮናስ አበበ በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሰረተ የሂሳብ ስራዎችን በተገቢው መንገድ በመገንዘብ ባሻገር ያለንን ዉስን በጀት በአግባቡ ተጠቅመን ዉጤታማ ለመሆን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ጥረት ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡ በገዘንዘብ ሚኒስቴር የፋይናንስ አሰራርና የአይቤክስ አተገባበር ቡድን መሪ አቶ ደረጀ መኮንን በበኩላቸው በአይቤክስ አተገባበር ወቅት አስፈላጊ የሆኑ የወጪና የተሰብሳቢ ሂሳብ መረጃዎችን በአግባቡ መመዝገብና የዉስጥ ኦዲት በግዢም ሆነ በንብረት ወጪና ገቢ በተቋሙ የሚፈጠሩ ስህተት ለማስቀረት ሚናቸው የላቀ ስለሆነ ልንጠቀማቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ስልጠናው የተሰጠው በገለፃ፣በቡን ውይይትና በአይቤክስ ትግበራ የተሰጠ ሲሆን በዚሁ ወቅት ከሰልጣኞችና ከአሰልጣኞቹ የተለያዩ አስተያየቶች፣ጥያቄዎችንና ምላሾችን በማንሸራሸር የሰላ ውይይት አድርገዋል፡፡ በሂደቱም ሰልጣኞች የመንግስት የሂሳብ አያያዝ ስረዓቶችን ተጠቅመው ትክክለኛና ወቅታዊ የሆኑ የፋይናንስ መረጃዎችን አዘጋጅቶ ለማቅረብ ወይም መቅረባቸዉን ለማረጋገጥ የሚያስችል ግንዘቤ መጨበጣቸዉን ሰልጣኞቹ በየበኩላቸው ከሰጡት አስተያየት ለመረዳት ተችሏል፡፡