Jinka University signs agreement with Ethiopian Wildlife Conservation Authority

The agreement was signed by Jinka University President Dr. Kusse Gudishe, and Mr. Nuru Yimer, Director of the Ethiopian Wildlife Conservation Authority, and General Manager of the Omo National Park. According to the agreement, the agreement will be extended from December 21, 2013 to the next three years from December 21, 2013.

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በምርምር ዙሪያ በትብብር ለመሰራት የውል ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል
ስምምነቱ የተፈፀመው የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅሜንት ኮሚቴ አባላት ባሉበት በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ እና በኢትዮጵያ ዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለስልጣን ተወካይና በኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ስራአስኪያጅ አቶ ኑሩ ይመር አማካኝነት እንደሆነም ታውቋል፡፡ስምምነቱም በዋናነት ያተኮረው በዱር እንሰሳት ዙሪያ በሚደረግ የምርምር ስራ ባለስልጣን መ/ቤቱ አስፈላጊዉን የገንዘብ ድጋፍ በማድረግና ሁለቱም አካለት ተቀራርበው በሂደቱ የጋራ መድረክ እየፈጠሩ የጋራ ተጠቃሚነታቸዉን ለማጎልበት ይህ ዉል ከተፈፀመበት ታህሳስ 21/2013 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀጣይ 3 ዓመት የሚቀጥል መሆኑንም የስምምነት ሰነዱ ላይ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡