Training on roadmap mapping and programs is being provided by the Office of the Vice President for Administration and Student Services at Jinka University. The training will be given in Turmi town of Hamer woreda and the first round is scheduled to be given today, February 25, 2013. Dr. Kusse Gudishe, President of the University, emphasized the role of all staff in fulfilling their responsibilities to implement the university’s vision.
Dr. Alemu Ailate, Vice President of Administration and Student Services of University, on his part, urged the trainees to actively attend the training and implement it in their respective departments.
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ለውጥ ፍኖተ-ካርታና ፕሮግራም ዙሪያ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
*******የካቲት 25/2013*******
በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት የተዘጋጀ የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ ፍኖተ ካርታና ፕሮግራሞችን የሚመለከት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው የሚሰጠው በሀመር ወረዳ ቱርሚ ከተማ ላይ ሲሆን በሁለት ዙር ለመስጠት ታስቦ የመጀመሪያው ዙር ዛሬ የካቲት 25/2013 ተጀምሯል።
ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት በመድረኩ መክፈቻ ላይ ሁሉም ሰራተኛ የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ ለመተግበር ሀላፊነቱን በብቃት መወጣት ትልቁን ሚና እንደሚጫወት በመግለፅ በመደጋገፍ የመስራት ልምድ እንዲዳብር፣ የተገልጋይ እርካታን በተቻለ መጠን ከፍ ማድረግና ቅድሚያ መስጠት ከስልጠናው በኋላ እንደሚጠበቅ አፅንዖት ሰጥተው አሳስበዋል።
ዶ/ር አለሙ አይላቴ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት በበኩላቸው ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃት ተከታትለው በቀጣይ ሁሉም በየስራ ክፍሎቻቸው ተግባራዊ እንዲያደርጉ በማሳሰብ ስልጠናውን አስጀምረዋል።