Jinka University launches leadership training for women leaders

The President’s Office in collaboration with the University’s Women, Children and Youth Affairs Directorate has launched a two-day leadership skills development forum for women leaders of South Omo Zone, Konso Zone, Alena Basketo Special Woreda. The forum was organized in Bena Tsemay Woreda Red Soil town. The training is being conducted by a professor from the Ministry of Science and Higher Education. He said the role of leaders is important for the success and failure of the people of a country and that leadership is a great responsibility.

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሴት አመራሮች የአመራርነት ክህሎት ማሳደጊያ የስልጠና መድረክ ተጀመረ።
*******የካቲት 22/2013********
የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ከዩኒቨርሲቲው ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለደቡብ ኦሞ ዞን፣ ለኮንሶ ዞን፣ ለአሌና ለባስኬቶ ልዩ ወረዳ ሴት አመራሮች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የአመራርነት ክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና መድረክ ተጀመረ። መድረኩ የተዘጋጀው በበና ፀማይ ወረዳ ቀይ አፈር ከተማ ላይ ሲሆን የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ የሴቶች ወደ አመራርነት መምጣትና እነሱን ማብቃት ለሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው በመግለፅ ስልጠናውን ከፍተዋል።
ስልጠናው እየተሰጠ ያለው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመጡት ፕሮፌሰር ያለው እንዳወቀ ናቸው። አሰልጣኙ ለአንድ ሀገር ህዝብ ስኬትም ሆነ ውድቀት የመሪዎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነና አመራርነት ትልቅ ሀላፊነት እንደሆነ በመግለፅ ስልጠናውን ጀምረዋል።