Jinka University discusses disruption of construction projects

Jinka University discusses disruption of construction projects with consulting firm and contractors
Jinka University is contracted by Atom construction, a local company that has contracted for fencing, bridge construction, and lighting and indoor asphalt construction. However, despite the fact that the works have not been completed yet, especially in Jinka town, the bridge to the university has been accelerating recently, but its performance has not exceeded 66.37 percent. The contractors and consultants blamed the deforestation, the shortage of cement supply and the high cost of some inputs, but neither the university nor the Ministry of Science and Higher Education’s 11 university construction project officials found it to be watertight.
During the discussion, issues related to the construction of classrooms and dormitories in the second and third floors were also raised. Dr. Kusse Gudishe, President of the Jinka University, said that if the 94.6 percent of the classrooms will be completed within a one week, efforts should be made to ensure that the 1st and 2nd year of students will call first week of January. He also presented a monthly plan and set a direction for evaluating its performance.

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው የግንባታ ፕሮጄክቶች መስተጓጎል ዙሪያ ከአማካሪ ድርጅቱና ኮንትራክተሮች ጋር ተወያይቶ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የአጥር፣የድልድይ፣የመብራት ዝርጋታና የግቢ ዉስጥ የአስፋልት ስራ ኮንትራት የወሰደው አተም የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ አስከ ዛሬ ስራዎቹን በገባው ውል አለማጠናቀቁ ብቻ ሳይሆን በተለይ ከጂንካ ከተማ ወደ ዩኒቨርሲቲው መሻገሪያ ድልድይ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ እየተፋጠነ ያለበት ሁኔታ ቢኖርም አፈፃፀሙ ከ66.37 በመቶ አልዘለለም፡፡የዙሪያ አጥር ግንባታ ስራዉም አንድ ሰሞን ሮጦ አሁን ላይ የተቀዛቀዘበት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ የዝናብ መብዛት፣የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትና የአንዳንድ ግብአቶች ዋጋ መናር ለስራው መጓተት ኮንትራክተሮቹና አማካሪ ድርጅቱ በምክንያትነት ቢያቀርቡም ዩኒቨርሲቲዉም ይሁን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ11 ዩኒቨርሲተዎች የግንባታ ፕሮጄክት አስፈፃሚ የቀረበው ምክንያት ዉሃ የሚቋጥር ሆኖ አላገኙትም፡፡
በውይይቱ ወቅት በግቢው ዉስጥ ለመማሪያ ክፍሎችና ለዶርሚተሪ በ2ኛና በ3ኛ ፌዝ እየተገነቡ ያሉት ህንፃዎችም ጉዳይ ተነስቷል፡፡ በተለይ አሁን ላይ 94.6 በመቶው የተጠናቀቀው የመማሪያ ክፍሎች ህንፃ በአንድ ሳምንት ዉስጥ ካልተጠናቀቀ በጥር የመጀመሪያው ሳምንት የሚጠሩት የ1ኛና የ2ኛ ዓመት ተማሪዎቻችን አቀባበል ላይ ችግር እንዳይገጥመን ብርቱ ጥረት መደረግ ይኖርበታል ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ የአተም ድርጅትም በተለይ የአጥር ስራዉና የድልድይ ግንባታው አሁን ከደረሰበት ተነስቶ ፍጥነቱን በእጥፍ በመጨመር የየወሩ እቅድ አቅርቦ አፈፃፀሙ እየተገመገመ የሚሄድበት አቅጣጫም አስቀምጠዋል፡፡