According to Dr. Kusse Gudishe, President of the University, who conducted the forum, the Exit Report of the 4th quarter of the 2012 fiscal year, presented by the University’s Internal Audit, was reviewed by financial, procurement and asset management leaders and experts as well as other stakeholders. He said the report was too late and did not take into account the delay of the first six months of the current budget year.
According to the University’s Internal Audit Directorate Director, Nibret Fekadu, the errors in the findings are mostly due to unsatisfactory purchases and payments, and both executives and executors should be corrected in accordance with the Internal Audit Proclamation, Regulations and Guidelines. .At the end of the meeting, the participants discussed the 20 audit findings and related issues for 2 consecutive days.
የተቋሙ የፋይናንስ አሰራር፣የግዢ አፈፃፀምና የንብረት አያያዝ መመሪያና ደንብ በጠበቀ መልኩ ብቻ መከናወን እንዳለባቸው የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ
በዩኒቨርሲቲው የዉስጥ ኦዲት የቀረበዉን የ2012 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የፋይናንስ አሰራር የዉስጥ ኦዲት ግኝቶችን የያዘ ኤግዚቲንግ ሪፖርት የፋይናንስ፣የግዢና የንበረት አስተዳደር አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የውይይት መድረክ ተገምግሟል፡፡መድረኩን የመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ እንደገለጹት 20 የዉስጥ ኦዲት ግኝቶችን አካቶ የቀረበው ሪፖርት በጣም የዘገየ ከመሆኑም ባሻገር የዚህ በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወር አፈፃፀም ሪፖረትን እንዳይዘገይ ከግምት ዉስጥ ያስገባ አይደለም ብለዋል፡፡በመሆኑም በዋናነት የሚመለከታቸው የፋይናንስ፣የግዢና የንብረት ክፍል አመራሮችና ባለሙያዎች በግኝቶቹ ላይ የተስተዋሉትን ስህተቶች የተቋሙን የተሻለ አፈፃፀም በሚያሳልጥ መልኩ ተናበው ማረም ይኖርባቸዋልም ብለዋል፡፡
ፋይናንስ በወቅቱ መረጃ ባለመስጠቱ የተፈጠረ መዘግየት ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው የዉስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ንብረት ፈቃዱ በግኝቶቹ ላይ የቀረቡት ስህተቶች በአብዛኛው በጥንቃቄ ጉድለት ባልተሟሉ መረጃዎች የተፈፀሙ ግዢዎችና ክፍያዎች በመሆናቸው በቀጣይም ተመሳሳይ ስህተቶች እንዳይፈጠሩ አስፈፃሚችም ሆኑ ፈፃሚዎች በዉስጥ ኦዲት አዋጅ፣ደንብና መመሪያ መሰረት ብቻ ሊታረሙና ሊፈፅሙ እንደሚገባ አሰገንዘበዋል፡፡
አንድ በአንድ የቀረቡትን 20 የኦዲት ግኝቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊዎች ለ 2 ተከታታይ ቀናት ከቤቱ የተነሱ አስተያየቶችና ጥያቀዎችን በማንሸራሸር የሰላ ውይይት አድርገዋል፡፡በመጨረሻም ቤቱ ከመድረኩ የተሰጠዉን በፋይናንስ አሰራርና የዉስጥ ኦዲት መመሪያና ደንብ የመገዛት ግዴታ ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ውይይቱን አጠናቋል፡፡