ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የኦክስጅን ሲሊንደሮችን አበረከተ።
****ግንቦት 24/2013******
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሰላሳ የኦክስጅን ሲሊንደሮችን ለጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል አበረከተ። ዩኒቨርሲቲው ባለፈው አመት ለዞኑ ማህበረሰብ በማገልገል ላይ ለሚገኘው ሆስፒታል በአለማችን ለተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መመርመሪያ መሳሪያና የኮቪድ ማእከል ማቋቋሙ ይታወቃል።
በዛሬው እለትም የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅና የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ በተገኙበት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚደንቶች መሳሪያዎቹን አስረክበዋል።
በርክክቡ ወቅትም የዞኑ ጤና መምርያ ሀላፊ እንዲሁም የሆስፒታሉ ስራአስኪያጅ ዩኒቨርሲቲውን በማመስገን ለወደፊትም እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በመጨረሻም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ ከአሁን በኋላም ዩኒቨርሲቲው በሚችለው አቅም አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን በማድረግ እንደሚቀጥልና ይህም ማህበራዊ ሀላፊነትን የመወጣት አንድ አካል እንደሆነ ገልፀዋል።
*እውቀት ለለውጥ”
Jinka university contributes oxygen cylinders to Jinka general hospital.
***** June 1st/2021*****
Jinka university has contributed thirty oxygen cylinders to Jinka general hospital.
It is known that JKU has build covid center, and gave covid-19 testing laboratory machine last year.
Around thirty cylinders have been contributed for the hospital in the presence of south omo zone health department head and the hospital’s principal.
Kusse Gudishe(PhD), president of JKU, has promised to continue the collaboration and to do together for the future with the hospital.
*Knowledge for Change*