The University of Jinka, the Ministry of Culture and Tourism and the Southern Regional Culture and Tourism Bureau, held a joint national conference on Indigenous traditional medicine and justice on December 11, 2012.
Statement by the Minister of Culture and Tourism, W/ro Buzena Alkadir, Minister of Culture and Tourism, symbolizing multicultural traditional medicine and conflict resolution systems in South China’s capital city, Jinka. It is unique that the country is the first to launch the ETRSS-1 enrichment satellite.
Prof. Gebre Yntiso, President of the Jinka University, who gave a welcoming speech to the participants of the conference, gave a brief overview of the conference, presentations, the exhibition, presenters and participants. He also said that these values play a major role in peace and development, adding that Ethiopia has a rich knowledge of indigenous peoples, following the success of Ethiopia as a multicultural country.
Eight articles were presented at the conference, and the providers are from the University of Addis Ababa, the Civil Service University, the Pastoral Institute (Health Ministry), and prominent scholars from Jinka University, who specialize in indigenous medicine. Participants were invited guests from all over the state, representatives from government agencies from the federal to district and city structure, house trusts, cultural medicine specialists and mediators.
Based on the presentations of the presentations, participants were discussed in detail and discussed in detail, and questions were answered from text providers and moderators. The Exhibition of Traditional Medicine and Crafts at the conference was visited by honorary guests and participants.
******************************************************************************************************************************
የተሳካ አገር አቀፍ ጉባኤ በጂንካ ከተማ ተካሄደ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣ የባህልና ቱርዝም ሚኒስቴርና የደቡብ ክልል ባህልና ቱርዝም ቢሮ በሀገር በቀል ባህላዊ መድሃኒትና የፍትህ ስርዓት ላይ በጋራ ያዘጋጁት አገር አቀፍ ጉባኤ ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓም በጂንካ ከተማ ተካሂዷል፡፡
ሀገር በቀል ባህላዊ መድሃኒትና የፍትህ ስርዓት ለዘላቂ ልማት!” በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደው ጉባኤ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የበርካታ ሀገር በቀል ባህላዊ መድሃኒቶችና የግጭት አፈታት ስርዓቶች ተምሳሌት በሆነችው የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ ጂንካ የተካሄደው ጉባኤ ሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ETRSS-1 የተባለችው የብልፅግና ሳታላይት ባመጠቀችበት ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ለጉባኤው ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ ስለጉባኤው ዓለማ፣ ስለሚቀርቡ ጽሁፎች፣ ስለተዘጋጀው ኤግዚቢሽን፣ ስለአቅራቢዎችና ተሳታፊዎች አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም አትዮጵያ የብዝሃ-ባህል ሀገር መሆኗን ተከትሎ ከተቼሩን ፀጋዎች መካከል ዘርፈ-ብዙ የሆነው ሀገር በቀል ዕውቀት ይገኝበታል ያሉት ፕሬዘዳንቱ እነዚህ እሴቶች ለሰላምና ለልማት ያላቸው ሚና የበዛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በጉባኤው 8 ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን አቅራቢዎቹ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከሲቭል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ ከፓሰተር ኢንስቲቱት (ጤና ሚኒስቴር) እንዲሁም ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ታዋቂ ምሁራንና ሌሎች በሀገር በቀል መድሃኒት ላይ ጥልቅ ምርምር ያደረጉና በዘርፉ አንቱ የተባሉ ጠቢባን ናቸው። ተሳታፊዎቹ ደግሞ ከሁሉም ክልል የተጋበዙ እንግዶች፣ ከፌደራል እስከ ወረዳና ከተማ መዋቅር የሚገኙ የመንግስት ተቋማት ተወካዮች፣ የቤቴ እምነት ተጠሪዎች፣ የባህላዊ መድሃኒት አዋቂዎችና አስታራቂ ሽማግሌዎች ነበሩ።
የቀረቡትን ጥናታዊ ጽሁፎች መነሻ በማድረግ ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን በማንሸራሸር በጥልቀት የተወያዩ ሲሆን ማብራሪያ ለሚሹ ጥያቄዎችም ከጽሁፍ አቅራቢዎችና አወያዮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ጉባኤውን አስመልክቶ የተዘገጀው የባህላዊ መድሃኒትና የዕደ ጥበብ ውጤቶች ኤግዚቢሽን በጉባኤው የክብር እንግዶችና ተሳታፊዎች ተጎብኝቷል።