Corruption is a dirty and evil thing, and it is also a scandal. University President Professor Gebre Yntiso said that while corrupt people have the capacity to use government money for the purpose and goal, we should prevent the nation and its families from harming themselves by doing such a shameful job, said the president.
Director of the University’s Ethics Monitoring Unit, who listed corruption and trends related to Human Resource Development and Secrecy, Finance, Procurement and Asset Management, said the role of accountability and transparency is the key to preventing corruption.
Participants indicated that the work being done to defend the perpetrators and the prosecution was not as accurate as they were based on their comments and questions raised by the institute, based on the discussion paper presented on the 15th anniversary of the university.
ሙስና ሀገርንና ትውልድን የሚገድል እኩይ ተግባር በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ሊጠየፈዉና በጋራ ሊከላከለው እንደሚገባ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ገለፀ::
ሙስና ቆሻሻና ክፉ ነቀርሳ ከመሆኑም ባሻገር ቅሌት የሚያስከትልም ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ገብሬ ይንቲሶ ሙሰኞች ሲስማሙ ደግሞ የመንግስት ገንዘብንም ለታለመለት ዓላማና ግብ እንደይውል የማድረግ አቅም እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡በመሆኑም ሙሰኞች የእራሳቸዉንና የቤተሰባቸዉን አንገት በእንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ሰራ አንገት ከማስደፋታቸው ይልቅ አስነዋሪ ድርጊቱን በጋራ በመከላከል ሀገርንና ተውልድን ማዳን ይኖርብናል ብለዋል ፕሬዘዳንቱ፡፡
በተቋሙ ከሰው ሀብት ልማትና ሰምሪት፣ከፋይናንስ፣ከግዢና ንብረት አያያዝ ጋር በተያያዘ የተስተዋሉ ሙስናዎችና አዝማሚያዎች የዘረዘሩት የዩኒቨርሲቲው የስነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ጥሩነህ ዳምጤ በበኩላቸው የስልጣን ተጠያቂነትና ግልፀኝነት ለሙስና መከላከል ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡
ተሳታፊዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲው ለ2ኛ ጊዜ የተከበረዉን የፀረ ሙስና ቀን ምክኒያት በማድረግ የቀረበላቸዉን የውይይት ሰነድ መነሻ በማድረግ በሰጡት አስተያየትና ባነሱዋቸው ጥያቄዎች በተቋሙ ተፈፀሙ የተባሉትን ሙስናና አዝማሚያዎች ባሻገር በመከላከሉና ፈፃሚዎቹን ለህግ አቅርቦ ተጠያቂ ለማድረግ የተሰራው ስራ በተፈለገው ልክ አለመሆኑን አመላክተዋል፡