According to the University of Jinka, the short training sessions offered to the executive and executive staff at different times would enhance the employee’s skills and enable them to perform better.
The University of Jinka has also provided training to staff of the Institute on Good Governance and Staff Code of Conduct. Speaking on the occasion, Director of Public and International Relations Directorate Zerigaw Manorgo said the training and skills will not only prevent internal and external governance problems, but also create a common capacity to deal with internal and external customers with a sense of service and professional ethics. The director, who is helping him, urged the staff to follow through on training and to focus on better change.
The director of the University’s Institutional Change and Good Governance Directorate, GENEMIE BUKIMI, said that the training aims to improve the performance of the institution in a positive manner. Moreover, the training is expected to play a significant role in creating the capacity to tackle the occasional good governance problem that has been observed in the institution over the last 2 years, he added.
The university’s administrative department of directors, team leaders, professionals and other staff have been involved in the training which has been organized in three phases since December 02, 2012.
*****************************************************************
በተለያዩ ጊዜያት ለአስፈፃሚዉና ለፈፃሚዉ የሚሰጡ አጫጭር የአሰራር ስልጠናዎች የሰራተኛዉን ክህሎት ከፍ በማድረግ ለተሻለ አፈፃፀም አቅም እንደሚፈጥሩለት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ገለፀ::
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በመልካም አስተዳደርና በሰራተኞች የሥነ ምግባር ኮድ መመሪያ ዙሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች ሰሞኑን ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘርጋው ማናርጎ ከዚህ ስልጠና ሰራተኛው የሚያገኘው ግንዘቤና ክህሎት የውስጥና የውጪ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮ ሲገኝም በቀላሉ ለመፍታት የሚያስችል የጋራ አቅም ይፈጥርለታል ብለዋል፡፡ከዚህ ባለፈ ሰራተኛው የውስጥና የውጪ ተገልጋዮቹን በአገልጋይነት ስሜት እንዲሁም በሙያ ሥነ ምግባር ታንፆ እንዲያገለግል ይረዳዋል ያሉት ዳሬክተሩ በመሆኑም ሰራተኛው ስልጠናዉን በአግባቡ ተከታትሎ የተሻለ ለውጥ ለማስገንዘብ እንዲተጋ አሳስበዋል::
ይህ ስልጠና በዋናነት የሚያተኩረው በተቋማችን መልካም አስተዳደር ዙሪያና በሰራተኞች የሥነ- ምግባር ኮድ መመሪያ ለሰራተኛው ተገቢውን ግንዛቤ በማስጨበጥ ላይ እንደሆነ የገለጹት የዩኒቨርሲቲው የተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገነሜ ቡቅሚ የስልጠናው ዋና ዓላማም በመልካም አስተዳደር ትግበራ የተቋሙን አፈጻጸም የተሻለ ደረጃ ለማድረስ ያለመ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ተቋሙ ውስጥ ባለፉት 2 አመታት አልፎ አልፎ የተስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል አቅም ለመፍጠርም ይህ ስልጠና ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ እንደሚታሰብም አቶ ገነሜ አክለው ተናግረዋል፡፡
ከታህሳስ 02/2012 ዓ/ም ጀምሮ በ3 ዙር ተከፋፍሎ እየተሰጠ ባለው ስልጠና የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ዘርፍ ዳይሬክተሮች፣የቡድን መሪዎች፣ባለሙያዎችና ሌለችም ሰራተኞች የተሳተፉበት ሲሆን ስልጠናው እስከ ታህሳስ 10 እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡