ግንቦት 19 ቀን 2011 ዓም በደቡብ ኦሞ ዞን የአርብቶ አደር ልማት ዙርያ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የጋራ ምክክር ተደረገ። በውይይቱ ላይ የተገኙት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛና መሀከለኛ አመራር፣ የሰላም ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የዩኤስ.ኤይድ (USAID) ልዑካን ቡድን፣ የደቡብ ኦሞ ዞን ሰክተር መ/ቤቶች ተወካዮችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ናቸው። ወርክሾፑ ያተኮረው በእርሻና እንስሳት ርባታ፣ በማህበራዊ አገልግሎቶች፣ በሰላምና ፍትህ፣ በግል ኢንበስትመንትና በግዙፍ የመንግስት ፕሮጀክቶች ላይ ሲሆን በነዚህ ዘርፎች ያጋጠሙ አብይ ችግሮች፣ መንስኤዎችና መፍትሔዎች በቡድን ውይይትና በጋራ ስብሰባ በዳሰሳ መልክ ተቃኝተዋል። ተሳታፊዎቹ በተለዩት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ ተከታታይ ግንኙነት ለማድረግና ጊዜው ሲደርስ ወደ ተግባር ለመግባት ተስማምተዋል። በዚህ ሂደት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ቁልፍ የማስተባበር ሚና እንዲጫወት መግባባት ላይ ተደርሷል።