ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተለያየ አይነት የስኳር ድንች ዝሪያዎችን ለማህበረሰቡ አሰራጨ።
**መስከረም 28/2014******
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚደንት ፅ/ቤት ከደቡብ ኦሞ የግብርና ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበር የተለያየ አይነት ያላቸው የስኳር ድንች ዝርያዎችን ለማህበረሰቡ ለናሙናነት አሰራጭቷል።
የናሙና ስርጭቱ የተደረገው በደቡብ አሪ ወረዳ በሼጲ እና ለባይፀማል ቀበሌዎች ለተወሰኑ አርሶ አደሮች ሲሆን የአተካከል ሁኔታውንም በዛሬው ዕለት ማለትም መስከረም 28/2014 ዓ.ም ስልጠና በመስጠት ስርጭት ተደርጓል።
የተሰራጩት የስኳር ድንች ዝርያዎች ላለፉት አመታት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የእፅዋት ሳይንስ መምህራን ከደቡብ ኦሞ ምርምር ማዕከል ጋር በትብብር ጥናት የተደረገባቸው ሲሆን ማህበረሰቡ ዘንድ ሲመረት የነበረው ‘Awasa 83’ በመባል የሚታወቀው የስኳር ድንች ዝርያ መሆኑንና አሁን የተሰራጩት ዝርያዎች ደግሞ ‘Awasa 09 እና በርኩሜ’ በመባል የሚታወቁ የስኳር ድንች አይነቶች መሆናቸውን ከተመራማሪዎቹ መካከል የሆኑት መምህር ብርሃኑ ስሜና መምህር ሁንዴሳ አብራርተዋል።
ተመራማሪዎቹ እንደገለፁት አሁን ማህበረሰቡ እያዘወተረው ከሚገኘው የስኳር ድንች ዝርያ ጋር ሲነፃፀር ሰፊ ለውጥ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚደንት ኤልያስ አለሙ(ዶ/ር) በበኩላቸው እንደዚህ አይነት መልካም ጅማሮዎችና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች የፅ/ቤታቸው ዋነኛ አላማው መሆኑን ገልፀው በዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ከመደርደሪያ ፍጆታነት ይልቅ ወደ ማህበረሰቡ የሚደርሱበት ዘዴዎችን በመጠቀም ሰፊ ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑትም መምህር ሰሙ ይታፈሩ እንደተናገሩት ዛሬ በዚህ መልኩ የተጀመረው የምርምር ውጤቶች ስርጭት ለቀጣይ ወደ ሌሎች አርሶአደሮች ዝሪያዉ በፍጥነት እንዲደርስ ያስችላል ብለዋል።
**//*********///********////********///*****
Jinka University distributes different varieties of sweet potato to the community.
***Oct.8/2021******
Jinka University office of the vice president for Research and Community Services in collaboration with South Omo Agricultural Research Center, has distributed various varieties of sweet potato to the community.
The new sweet potatoes adaptation have been studied by JKU plant science department instructors in collaboration with South Omo Research Center and, the new yields were distributed to farmers in Shep’i and Baitsemal kebeles.
According to Mr. Birhanu Sime and Mr. Hundesa’s explanation, there is a significant difference among in the new variety of the sweet potatoes and potatoes that have being planted in the community. So, the more will be done to transfer for the society as of them.
Elias Alemu(PhD), Vice President for the University’s Research and Community Services office, said such technology transfer activities and disseminating research outputs are the main objective of his office.
Director of the Community Service Directorate, Mr. Semu Yetaferu on his part also said the distribution of research results, which started today, will enable to reach for other farmers for the future.