የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በአራት ትምህርት ቤቶች ከአንደኛ እስከ አስረኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡ የድጋፉ ዝርዝር 150 ቦርሳዎች፣ 3300 ደብተሮችና 600 እስክብርቶዎች ሲሆኑ አጠቃላይ 150 የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለዚሁ ድጋፍ ዩኒቨርሲቲው መቶ ዘጠና ሺህ ብር ወጪ ማድረጉን በመግለጽ ለመማር ፍላጎት ኖሯቸው ቤተሰቦቻቸው አቅሜ ደካማ በመሆናቸው የተነሳ የሚቸገሩ ተማሪዎችን መደገፍ የወገን ድርሻ መሆኑን አውስተዋል። እርስዎም በአቅራቢያዎ ለሚገኝ መሰል ተማሪ እጅዎን ይዘርጉ።
“እውቀት ለለውጥ”