Jinka University signed two memorandums of understanding today February 17, 2013 E.C
Jinka University has signed a memorandum of understanding to work with two different parties. The agreement was reached in collaboration with the South Omo Zone Youth Federation and the Mago National Park Offices.
The agreement with the Office of the Youth Federation aims to provide training and capacity building for the zone’s youth.
“Knowledge for Change”
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የመግባቢያ ሰነዶችን በዛሬው እለት የካቲት 17/2013 ተፈራረመ።
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ከተለያዩ አካላት ጋር አብሮ ለመስራት የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። ስምምነቱ የተደረገው ከደቡብ ኦሞ ዞን የወጣቶች ፌዴሬሽንና ከማጎ ብሄራዊ ፓርክ ፅ/ቤቶች ጋር በትብብር ለመስራት ነው። ከወጣቶች ፌደሬሽን ፅ/ቤት ጋር የተካሄደው የስምምነት ውል የዞኑን ወጣቶች ብቃት ለማሳደግ የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ለመስጠትና ሁለንተናዊ ስብዕናን ለመገንባት ያለመ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከማጎ ብሄራዊ ፓርክ ፅ/ቤት ጋር ፓርኩን በመንከባከብና የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ከፓርኩ የሚገኘውን ጥቅም ለማሻሻል በትብብር ለመስራት ነው ስምምነቱ የተደረገው።