በጂንካ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የተነሱ የመልካም አስተዳደርና የአሰራር ችግሮች በሂደት እንደሚፈቱላቸው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ገለጹ
በ12/04/2013 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲዉን መምህራን አሰባስበው መምህራንን አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲው በሚስተዋሉ የተለያዩ ችግሮች ዙሪያ መምህራንን አወያይተዋል፡፡በውይይቱ ወቅትም ከመምህራኑ የተለያዩ የመልካም አስተዳደርና የአሰራር ችግሮች እንዲሁም መምህራንን በምርምር ዘርፉ በፍትሃዊነት ከማሳተፍ አንፃር ክፍተቶች እንደሚስተዋሉና ተያያዥ የሆኑ በርካታ ተግዳሮቶች በሂደት በአብሮነት አንደሚፈቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ አስገንዝበዋል፡፡
በተመሳሳይ በቀን 13/04/2013 ዓ.ም የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች በዩኒቨርሲቲው በየዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች እንደፈቱላቸው ጠየቁ
የዩኒቨርሲቲውን የአስተዳደር ሰራተኞች አሰባስበው ከዩኒቨርሲቲው 4ቱ ም/ፕሬዚዳንቶች ጋር በመሆን ከ70 መቶ በላይ የሚሆኑ የአስተዳደር ሰራተኞችን ያወያዩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኩሴ ጉዳሼ ከሰራተኞቹ በዋናነት የተነሱትን የሰራተኛው የትምህርት ዕድል አሰጣጥ፣መመሪያና ደንብን ያልተከተሉ ምደባዎች፣ቅጥሮች፣ከግዢ ጋር የየተያዙ ችግሮችና ተያያዥ ተግዳሮቶች እንደየክብደታቸዉና ቅለታቸው በሂደት የሚፈቱ እንደሆኑና እነዚህንም ችግሮች መፍታት ለአንድ ወገን ብቻ የሚተዉ ሳይሆን ቅንጅታዊ አሰራርን የሚጠይቁ ናቸው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ከቤቱ የተነሱ በርካታ ጥያቄዎች የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ከመድረኩ ምላሽ ከተሠጠባቸው በኋላ መግባባት ላይ በመድረስ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡