Soil and water conservation work will benefit the local community beyond research

Leaders, faculty and other stakeholders from the university toured the campus and outside the campus for research and community service activities. Dr. Tekle Olbamo, Director of Research Directorate, on his part said the work is being done to identify the problems encountered during the field visit. “We are working to transfer research project work to the community,” he said.
Argachew Bochena, Director of the Community Service Directorate, said the community’s ongoing soil and water conservation project in Kaisa Kebele, by training and coordination with the community has reduced the risk of flooding in the area. Semu Yitafereu, Dean of the University’s College of Agriculture and Natural Resources, on his part, said he has no doubt that the challenges faced during the visit will be overcome if the university’s natural resource conservation and research activities are carried out. According to Kafa Ata, one of the beneficiaries of the project, the community is producing a variety of crops without any risk.

በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ለምግብነትና ለመድሃኒትነት የሚዉሉ አፀዋት እንዲሁም የአፈርና የዉሃ ጥበቃ ስራ ለምርምር ስራ ከማስተማሪያነት አልፎ የአከባቢዉን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ተገለፀ

ከዩኒቨርሲቲው የተወጣጡ አመራሮች፣መምህራንና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢና ከግቢው ዉጪ በምርምርና ማህበረስብ አገልግሎ የተከናወኑ ተግባራትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡የዩኒቨርሲቲው ተግባራት ለመቃኘት የተደረገዉን ጉብኝት ያስጀመሩት የአካዳሚከ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንትና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ኃይለጎርጊስ ቢራሞ በመስክ ጉብኝቱ የተሻሉ አፈፃፀሞችን አስፋፍቶ ለምርምር ለመጠቀምና ማህበረሰቡንም በችግር ፈቺ ምርምር ዉጤት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ተጠነከክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡በመስክ ጉብኝቱ ወቅት የገጠሙ ችግሮችን በመለየት የተሻለ ስራ ለመስራት ያለመ ነበር ያሉት የምርምር ዳይሬክቶሬት ዲይሬክተርና የምርምርና “””ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ተክሌ ኦልባሞ በበኩላቸው በግቢው ዉስጥና ከግቢው ዉጪ በተለያዩ ቦታዎች እየተሰሩ ያሉት የምርምር ፕሮጄክት ስራዎች ወደ ማህበረሰቡ አገልግሎት ለማሻገር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቡን በማሰልጠንና በማስተባበር በካይሳ ቀበሌ እያከናወነ ያለዉን የአፈርና የዉሃ ጥበቃ ፕሮጄክት የአከባቢው ማህበረሰብ ቀደም ሲል ከነበረበት ከዛሬ ነገ ጎርፍ ይበላኛል ስጋትን ያስቀረ ነው ያሉት የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አርጋቸው ቦቸና ቀደም ሲል በደለል የተሞላ አከባቢ ዛሬ ላይ ማህበረሰቡ ጎርፉን የማቀብ ስራዉንና ሰብል የማምረት ስራዉን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡በዩኒቨርሲቲው የግብርናና የተፈጥሮ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ ሰሙ ይታፈሩ በበኩላቸው የኒቨርሲቲው በሰራቸው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራና በዘርፉ እያከናወናቸው ባሉ የምርምር ስራዎች በጉብኘት ወቅት የታዩ ተግዳሮቶቻቸዉ ከተቀረፉ ዉጤታማ እንደሚሆኑ አልጠራጠርም ብለዋል፡፡
በግቢው ዉስጥ የተተከሉ የመድሃኒትና እፀዋት ችግኞች እንዲሁም የአፈርና የዉሃ ጥበቃ ፕሮጄክት ከማስተማሪያነት አልፈው ለማህበረሰቡ አስፈላጊዉን አገልግሎት በተፈለገው ልክ እስከሚሰጡ በዘርፉ የተሰማሩ ተመራማሪዎችንና መምህራን የየበኩላቸዉን ጥረት እንደሚያደርጉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡በአከባቢው የፕሮጄክቱ ተጠቃሚ ከሆኑ ማህበረሰብ አንዱ የሆኑት አርሶ አደር አቶ ካፋ አታ ዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቡን በማስተባበር ባከናወነው የጎርፍ መከላኪያ የጋቢዮን ስራ በማስፋፋት ማህበረሰቡ ያለምንም ስጋት የተለያዩ ሰብሎችን እያመረተ እንደሚገኝ በሰጡት አስተያየት አመላክተዋል፡፡