በድረ ገጽ ተደራሽ ለሚሆኑ ተማሪዎች መጽሐፍት ተፖስቷል
*********************************************
በአለማችን በተከሰተውና ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ በሚገኘዉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን በሽታውን እንድከላከሉና በተቻላቸው መጠን እያነበቡ እንዲቆዩ አቅጣጫ መቀመጡ ይታወሳል። ነገር ግን በርካታ ተማሪዎች የሚነበብ መጽሐፍት ላይኖራቸው ይችላል። ለሁሉም ተማሪዎች ተደራሽ መሆን ባይቻልም በድረ ገጽ መረጃ ሊያገኙ ለሚችሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዉ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ከኮሌጅ ዲኖች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት በMoSHE ድረ ገጽ አዘጋጅነት የተጫኑ የመማሪያና የማጠቃሻ መጻሕፍት ሁሉም ተማሪዎች ማገኘት እንድችሉ አቅጣጫ አስቀምጧል። በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ድረ ገጽ https://www.jku.edu.et በተጨማሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒሲቴር ያዘጋጃቸውን ከዚህ በታች የተገለጹትን ዲጂታል ላይብረሪ መጠቀም ይችላሉ።
በአገራችን የኢንተርነት ሽፋን በጣም ውስን እንደሆነና የገጠር ተማሪዎችም ሆኑ ከድሃ ቤተሰብ የወጡ የከተማ ልጆች በድረ ገጽ መረጃ ማግኘት እንደምቸገሩ ይገባናል። ስለዚህ ተማሪዎች ሲመለሱ ሃንድአውት ይሰጣቸዋል። አሁን ሳይረበሹ በእጃቸው ሊገባ የሚችለውን ብቻ በማንበብ ከበሽታው ተከላክልው በጤና እንዲመለሱ እየተመኘን እርስ በርስ መረጃ በመለዋጥ እንዲረዳዱ እንመክራለን።
ዕውቀት ለለውጥ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ