National Conference on the Field of Indigenous Medicine

According to the Office of the Vice President of Research and Community Services of the Jinka University, the recent National Conference on Gender in the field of Indigenous medicine and justice was successful and important.
The University of Jinka, in collaboration with the Ministry of Culture and Tourism and the Southern Regional Bureau, said the conference on indigenous medicine and justice was very successful and important. We will continue to strengthen research and research based on input from the conference as it creates great opportunities for promoting, developing and developing indigenous knowledge in the region, he said.

Thanks to the committee members who worked hard at the university, from the chapter to the end of the chapter, thanks to the committee members, Dr. Tekle Olbamo, who has learned from the conference on his part of the tradition, has traditionally embraced the traditional herbal products. A good partner who can greatly assist in passing on knowledge of a scientifically-assisted country to transfer it to the next generation and focus on the youth. PM said that.
// Knowledge for Change !! //

**************************************************************************

በሀገር በቀል መድሃኒትና የፍትህ ስርዓት ዙሪያ በቅርቡ በጂንካ ከተማ የተካሄደው ሀገራዊ ጉባዔ የተሳካና የጎላ ፋይዳ እንደነበረው የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት ገለፀ
*******************************************
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከደቡብ ክልል ባ/ቱ ቢሮ ጋር በመተባበር በሀገር በቀል መድሃኒቶችና የፍትህ ስረዓት ዙሪያ ያደረገው ጉባዔ እጅግ የተሳካና ፋይዳዉም የጎላ እንደነበረ የገለጹት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ዲቃሶ ኡምቡሼ በቀጣይ የበርካታ ብዝሃ ሕይወትና ባህል ማዕከል በሆነችው ደቡብ ኦሞ ከጉባኤው የተገኙ ግብዓቶችን መነሻ በማድረግ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች በዞኑ ሀገር በቀል እውቀቶችን ለማስተዋወቅ፣ለማጎልበትና ለማልማት ከፍተኛ ዕድል የሚፈጥሩ በመሆናቸው አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ጉባዔው የተሳካ እንዲሆን ከዝግጅት መዕራፉ እስከ ፍፃሜው ከዞንና ከከተማ አስተዳደሩ ተወጣጥተው በዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የኮሚቴው ዓባላት በዩኒቨርሲቲው ስም ከፍተኛ ምስጋናቸውን ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተክሌ ኦልባሞ በበኩላቸው ከጉባዔው የተማርናቸው በየአከባቢው በተለይ በወጣቱ ዘንድ የተረሱ ባህላዊ መድሃኒቶችና የግጭት አፈታት ስረዓቶች ያላቸዉን ፋይዳ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍና ወጣቶችም ወደ ዘርፉ ትኩረት በመስጠት በሳይንሳዊ ምርምር የታገዘ ሀገር በቀል እውቀት እንዲያጎለብቱ በከፍተኛ ሁኔታ የሚረዳ መልካም አጋጣሚ እንደነበረ ገልፀዋል፡፡
// እውቀት ለለውጥ!! //