Jinka University announced that it has imposed penalties on abusive students

Despite being a symbol of peace at the University of Jinka, in early November 2012, a group of students stormed into a classroom with a student-media program created by students, inflicted bodily harm or death, and attempted to stir up a restaurant by disrupting the diner. It is remembered that 24 students have been charged with disciplinary offense.

The university’s administration and students’ service has, in its view, been able to settle the 3-year felony charge for the defendants in its efforts to resolve the allegations made by the relevant stakeholders.

1. Number of five defendant students have been found guilty of first degree offense and suspended from school for 2 years;

2: Number of  seven defendants  students have been found guilty of high school on the charges and have been sentenced to one year for expulsion.

3. Number of  nign defendants students have been found guilty information from the Office of the University’s Office of Student Affairs and Student Services confirmed that three of the defendants were found guilty of third-degree felony charges and the remaining 3 defendants were acquitted. It should be noted that this decision not only alerts students who have made a decision from a severe written warning to expulsion, but also warns other students in no way to end their own and their family’s dreams.

******************************************************************************

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ በጥፋተኛ ተማሪዎች ላይ ቅጣት የወሰነ መሆኑን አስታወቀ
***************************************
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ተምሳሌት እንደሆነ ቢታወቅም በ2012 ህዳር ወር መጀመሪያ ላይ የተወሰኑ ተማሪዎች በተማሪዎች በተዘጋጀ የሚኒ-ሚዲያ ፕሮግራም ጋር በተገናኘ ሁከት የፈጠሩ፣ የአካል ጉዳት ወይም ሞትን ሊያስከትል የሚችል ፌሮ ብረቶችን ወደ መኝታ ክፍል ያስገቡ፣ መመገቢያ አዳራሽ ምግብ በመድፋት ብጥብጥ ለማስነሳት የሞከሩና ብሔር-ተኮር ቅስቀሳ ያደረጉ በድመሩ 24 ተማሪዎች የዲሲፒሊን ጥፋት ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበረ ይታወሳል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተማሪዎቹ ለተመሰረተው ክስ በቂ ማስረጃ በማሰባስብ እልባት ለመስጠት ባደረገው ጥረት ለተከሳሽ ተማሪዎቹ በ3 ደረጃ የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷዋቸዋል፡፡በዚሁ መሰረት፡-
1ኛ/ 5 ተከሳሽ ተማሪዎች በተከሰሱበት ጉዳይ የመጀመሪያ ደረጃ ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋግጦ ለ2 ዓመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ፣
2ኛ 7 ተከሳሽ ተማሪዎች በተከሰሱበት ጉዳይ የ2ኛ ደረጃ ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋግጦ ለ1 ዓመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ መወሰኑና
3ኛ/ 9 ተከሳሽ ተማሪዎች በተከሰሱበት ጉዳይ የ3ኛ ደረጃ ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋግጦ ከባድ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸውና የተቀሩት 3 ተከሳሽ ተማሪዎችም ከተመሰረተባቸው ክስ ነፃ መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ይህ ዉሳኔ ደግሞ ከከባድ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ከትምህርት ገበታ ማገድ ውሳኔ ላይ የደረሱ ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ተማሪዎች በማንኛዉም መልኩ ወደ ጥፋት ገብተው የራሳቸዉንና የቤተሰባቸዉን ህልም እንዳያጨልሙ የሚየስጠነቅቅና የሚያስተምር እንደሆነ መታወቅ ይኖርበታል፡፡